Thumbnail for Prof. Mesfin Woldemariam’s historical speech in Seattle - May 27, 2017 by Ecadf Ethiopia

Prof. Mesfin Woldemariam’s historical speech in Seattle - May 27, 2017

Ecadf Ethiopia

43m 6s2,800 words~14 min read
Auto-Generated

[0:00]ደህና ይስጥልኝ እኔ ስካሁን ድረስ የሰማሁት

[0:10]በእውነቱ ይሄ ስብሰባ በዋና ዋና መሰረታዊ ሀሳቦችን ተገለጠ ይመስለኛል በጸሎትም ስም ይሁን በሌላ መንገድ የሚያስፈልጉት አንኳር አንኳር ሀሳቦች ተነግረዋል ያንን እንግዲህ እኔ እንደው ላገላብጠው ብዬ ነው። ከዛ በፊት ግን የራሴን ጸሎት አለኝ።

[1:07]የሁላችንም አምላክ ሆይ እባክህን ልዩነታችንን የት አንድነታችንን ብርታት አድርግልን።

[1:31]እባክህን አምላካችን ልባችንን ለፍቅር እና ለስምምነት አእምሮአችንን ለበጎ ሀሳብ እና ለቅንነት አዘጋጅልን። በእውነት እንድንመራ መንፈሳዊ ወኔ ስጠን።

[2:10]እኔ በ1996 ዓመተ ምህረት ይመስለኛል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር ዛሬ መኖሩን እንጃ ራእይ 2020 በሚል አጠቃላይ ርእስ ስብሰባ አዘጋጅቶ ነበር። በዛ ስብሰባ ላይ እኔ ያቀረብኩት ጽሁፍ ውስጥ እልም ያለ ባቡሩ የሚል ርእስ ሊሰጠው የሚችል የቃላት ምስል አሳይቼ ነበር። ቃል በቃል ሳይሆን ያልኩት እንደሚከተለው ነው። ባቡሩ ይሄዳል። ተሳፋሪዎቹ በቀር ካሀ የጎሳ አጥር ተለያይተው ይተራመሳሉ። የባቡሩን ነጂ የተሳፋሪዎቹ ትርምስ አስፈርቶት ክላሹን ይዞ ፊቱን ወደ ተሳፋሪዎቹ አዙሮ ራሱን ይጠብቃል። ባቡሩ ያለነጂ ይገሰግሳል። ነካ ማርጄቴን ረሽቼው ነበረ። ይሄን አሁን በቅርቡ መነጽር አስፈላጊ መሆኑን ተረድቻለሁኝ።

[3:42]ባቡሩ ያለነጂ ገሰግሳል። ባቡሩ የሚገሰግስበትን አቅጣጫ ነጂው አያይም። ተሳፈሪዎቹ ያያሉ። ተሳፋሪዎቹ ባቡሩ ወደ ገደል ሲሄድ እየታያቸው ይጮሃሉ። ጩኸታቸው ነጂውን ይበልጥ ያስደነብረዋል። እሱ ግን ፊቱን አዙሮ ስለተቀመጠና በፍርሃት የተጠመደው በተሳፋሪዎቹ ግርግር ስለሆነ ገደሉን አያይም።

[4:17]ባቡሩ ገደል ይገባል። ዛሬ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 2017 ነውና ትንቢቱ መስራት አለመስራቱን ለማየት ሶስት አመቶች ያህል ይቀረናል። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቃታል? ገደሉም እንዳለ ነው። በአሁኑ ጊዜ በእውነት የማሰብ ደረጃ ላይ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ስለ ሀገሩ ታሪክ እና ስለ ህዝቡ ኑሮ ማሰቡ የማይቀር ነው። እዚህ ከደረሰ ደግሞ ሁለት ጥያቄዎች የማይቀሩ ናቸው። አንደኛ የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገረ መንግስት ውስጥ መኖር ከጀመረ በሺ የሚቆጠሩ የታሪክ አመታት አስቆጥሯል። ስልጣንን ለመግራት ስልጣን ለማስያዝ ስርአት ለማስያዝ ያልቻለው እንዴት ነው። ሁለተኛ በእውቀት እና በኑሮ ለመሻሻል እና ከአመት ወደ አመት ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያድግበት የማያድግበት ምክንያት ምንድነው። ወይም እንዴት ቆሞ ቀር ሆነ። እነዚህ ጥያቄዎች ከአእምሮው ያልፈለቁበት እና ያላስጨነቁት ኢትዮጵያዊ ማሰብ አልጀመረም። እኔ የህይወት አላማ አድርጌ የያዙት ለነዚህ ሁለት ጥያቄዎች መልሶችን ማግኘት ነበር። ነገር ግን በአጼ ሀይለ ስላሴም ሆነ በደርግ የአገዛዝ ዘመኖች የወያኔን ፍጹም ጸረ እውቀት የሆነ አገዛዝ አላነሳሁም። በአእምሮ ስርአት ተሰማርቶ የሚያውቅ ሁሉ እንደሚገነዘበው ከየውጭ ሀገሩ የተለቃቀመውን ስርአተ ትምህርት እየደረቱ የልጆችን አእምሮ ማጨቅ የከፍተኛ ትምህርት ሆነ። ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያ ነፍስ የሚነካውን ነገር ማንም ሊዳስሰው ቀርቶ ሊደርስበት የቻለ አልነበረም። የኢትዮጵያ ባህላዊ ትምህርት እና የኢትዮጵያን ዘመናዊ ትምህርት እውነተኛ መልኮች እናስታውስ። ከምንኖርበት ከደሳሳ ጎጆ ወጥተን ወደ ባህላዊ ትምህርት ቤት ስንሄድ የምንማረው ውጭ በፀሀይ ላይ ወይም በዛፍ ስር ነው። ከባህላዊ ትምህርት ቤት ጎጆአችን ይሻላል። ስለዚህም ጎጆአችን ቤታችን ይናፍቀናል። ከጎጆአችን ወጥተን ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ስንደርስ ግን የምንገባው ልዩ የግብ ቤት ውስጥ ነው። የምንቀመጠው በወንበር ላይ ነው። እዚያ ሆነን ጎጆአችን አይናፍቀንም። እንደውም ሳንረሳው አንቀርም። ተመልሰን ወደ ጎጆአችን ባንሄድም ደስ ይለናል። አመቶች እያለፉ ሲሄዱ ጎጆአችን በአካልም በመንፈስም እየራቀች ትሄዳለች። ምግባችን ይለወጣል። ልብሳችን ይለወጣል። አነጋገራችን ይለወጣል። ዛሬ የደረስንበት በቋንቋችን እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም የሚሉት ቃላት ጠፍተው በእንግሊዝኛ ቃላት የተተካበት ነው። ማዘር ፋዘር ሲስተር ይላሉ። ሽማግሌዎች ሳይቀሩ። በአጭሩ ያልሆነውን ለመሆን እንጥራለን። እንግዲህ ዘመናዊ ትምህርት የምንለው ከቤታችን ከጎጆአችን እና ከቅርብ ዘመዶቻችን ከጎረቤታችን ከማህበረሰባችን እየለየን እያራቀን የትም ሳያደርሰን የተማሩ ሰዎች ያሰኘናል። ሀገር የሌላቸው ወላጆች የሌሏቸው ዘመዶች የሌሏቸው ጎረቤቶች እና ማህበረሰቦች የሌሏቸው የተማሩ ሰዎች። በእንደዚህ ያለው ሁኔታ የተማሩ የሚለው ሆኖ ሰዎች የሚለው ቃል ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ከመሆን ወደ መምሰል ይጠጋሉ። የተማሩ ይመስላሉ። ሰዎች ይመስላሉ እንጂ አይደሉም ለማለት ይቃጣናል። እናቶቻቸውና አባቶቻቸው የሞቱለት እና ያወረሷቸውን አላማ የካዱና የከዱ ምን ሀገር አላቸውና ይገነባሉ። ምንስ ወገን አላቸው። ግራ ሲገባቸው በሰው ሀገር ተቀምጠው ልብ ወለድ የጎሳ አጥር የሚያጥሩ ናቸው። የጎሳ አጥር መቆሚያ እንደሌለው ቆም ብለው ለአንድ አፍታ ያላሰቡት ሰዎች የጎሳ ፈረስ እየጋለቡ ለስልጣን ይፎካከራሉ። ሱማልያንን እና የመንን የሌሎች ብዙ ሀገሮችን ፍዳማ ያዩ አይታያቸውም። ያለፈውን መጥፎ ታሪክ ዝቃጭ ይዘው ለወደፊቱም ሊቀጥሉ ይመኛሉ። እንኳን በኢትዮጵያ እና በኒውዮርክም ሆነ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ መጥፎ ታሪክ አይደገምም። የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩነቱን በአንድነት ቋጥሮ ጉራማይሌ መልኩን ጉራማይሌ ሁለንተናውን ጠብቆ የብዙ ሺህ አመታት ታሪኩን ያድሳል። ታሪኩን ያድሳል ስንል አስቀድሞ ህዝቡ ማለት የዛሬው ትውልድ ራሱን ያድሳል ማለታችን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በተባባች ለውጥ እየተለዋወጠ ጉራማይሌ ኢትዮጵያዊነቱን ሳይለቅ በዘመናዊ የዜግነት አብሮነት ይተሳሰራል። ማለት ነው። ለብዙ ሰዎች አንድነት እና ልዩነት ተቃራኒ አቋሞች መስለው ይታያሉ። ነገር ግን ልዩነት ከሌለ አንድነት ምን ትርጉም አለው። አንድነት ከሌለስ ልዩነት ምን ትርጉም አለው።

[10:43]የዜጎችን አንድነት በጎሳ ለመበተን የሚፈልጉ ሰዎች ካለፈው በራሳቸው የስልጣን ምኞት ላይ በማተኮራቸው የጎሳ አንድነት በሚመስላቸው ውስጥ ልዩነት መኖሩን አያውቁም። አንድነት እያሉ የሚጮሁትም የልዩነቱን የባህሪ ደባላነት አይረዱም። የኢትዮጵያ ህዝብ በረጅም ታሪኩ የሚያረጋግጠው ሁሌም በግፈኛ አገዛዝ ስር እየተዋረደ እና እየተበዘበዘ በድህነት ቢኖርም ገዢዎቹ ለክብራቸው እና ለስልጣናቸው በጦርነት እያጋተሙ ቢያጋድሉትም እርስ በእርሱ እየተጋባ እና እየተዛመደ ኖሯል። ለዚህ ነው። አጼ ሀይለ ስላሴን ኦሮሞነት ሳናውቅ የኖርነው። ለዚህ ነው። በላይ ዘለቀን እና ብዙዎች ሌሎቹም ኦሮሞ መሆናቸውን የማናውቀው።

[11:53]ዛሬ ሀይለ ማርያም ደሳለኝ የመጀመሪያው ወላይታ ባለስልጣን የሚመስላቸው በአጼ ሀይለ ስላሴ ዘመን የነበረውን እውነት ስለማያውቁ ነው።

[12:15]የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን የካበው በሰውነቱ ላይ ነው። ዜግነቱን የካበው ደግሞ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ነው። አገዛዞች ላይ ተገዛ በሚል የግፍ አገዛዝ ሰልጥ እንድናናቅ ለማድረግ ሞክረዋል። በመቶንም ተሳክቶላቸዋል። የአገዛዙ ቁንጮዎችም ቢሆኑ ስልጣናቸውን ለማጠናከር ግዛታቸውን ለማስፋት ሲሉ እርስ በእርሳቸው እስከኛው ዘመን ድረስ የፖለቲካ ጋብቻ በሚባለው ይተሳሰሩ ነበር። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የተጋባና የተዛመደ ነው። ዛሬም በአደባባይ ባእድ እንዲባባል ከተደረገም በኋላ ዝምድናውን እና ትስስሩን አላቆመም።

[13:04]የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ላይውንም እንኳን ስንፈትሸው ከጎሳ ይልቅ የከበደ ተጽኖ የነበረው ሀይማኖት ይመስለኛል። ሆኖም ሀይማኖት የኢትዮጵያን ህዝብ የተፈለገውን ያህል ሊከፋፍል አልቻለም። ኢትዮጵያውያን በለውጥ እናምናለን። ኦሪትን ያለምንም ችግር ተቀብለን የራሳችን አድርገናል። ክርስትናን ያለምንም ችግር ተቀብለን የራሳችን አድርገናል። እስልምናን ያለምንም ችግር ተቀብለን የራሳችን አድርገነዋል። ሶስት አለም አቀፍ ሀይማኖቶች ሶስቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ሀይማኖቶች አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ሀይማኖቶች በብዙ ሀገሮች ሲተከሉ የብዙ ሰዎች ህይወት ጠፍቶ የሰው ደም እንደ ጎርፍ ሀገሩን አከረፍቶ ነው። በኢትዮጵያ ይህ አልሆነም። ሶስቱን ሀይማኖቶች በተመለከተ ሶስቱም ተቃቅፈው የተኙበት ወሎ ነው። ወሎ የፍቅር ሀገር ነው። አንዱ ሀይማኖት ብቻውን ጨምድዶ ለመያዝ ሲሞክር የኢትዮጵያ ህዝብ አይወድም። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚስማማው ያዝ ለቀቅ ነው። መጨነቅን አይወድም። ለየብቻ ቆራጭ ፈላጭ ለመሆን ለኦሪታውያንም ለክርስትናም ለእስልምናም አልሆነም። ሶስቱም ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን ሞክረዋል። ሶስቱም አልተሳካላቸውም። የሶስቱም ሀይማኖቶች ታሪክ ብቻ የኢትዮጵያን ህዝብ ባህሪ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት እና የኖሮ መሰረት በሚገባ ያስተምር ነበር። ከተከታታይ ትውልዶች ውስጥ ይህንን ትምህርት የቀሰመና ለኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ በመሰረተነት የተከለ ትውልድ እስካሁን አልተፈጠረም።

[15:04]ያሳዝናልም ያስገርማል። የሚያሳዝነው የኢትዮጵያ ህዝብ በሶስት ሺህ አመታት ታሪኩ ካለፈው እየተማረ ስህተቱን እያረመ አለመሻሻሉ ነው። የሚያስገርመው ኢትዮጵያ የአንድ ፈላጭ ቆራጭ ሀይል ሀገር እንድትሆን እንዳለ የኢትዮጵያ ህዝብ የማይፈልግ መሆኑን በትጋትና በቆራጥነት ማሳየቱን ነው። አንዱ ሀይማኖት ጨምድዶ ሲይዘው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይፈቅድ ሁሉ አንድ የግፍ አገዛዝም ጨምድዶ ሲይዘው አይወድም። የኢትዮጵያ ህዝብ ያኮርፋል። ቅም ይይዛል። አድፍጦ ምቹ ጊዜን ይጠብቃል። ጊዜው ሲደርስ ሳምባ ይፈርስ እያለ ብዙ ጊዜ ይፈጅበት ይሆናል። ለምን የታፈነ ህዝብ ስለሆነ መሰብሰብ አይችልም። ሀሳቡን በግልጽ መምከር መመካከር አይችልም። መደራጀት አይችልም። መታፈኑንም ለመቋቋም የኢትዮጵያ ህዝብ ዘዴ ይፈጥራል። እያንዳንዱ ሰው ለየብቻው ቅሙን ቋጥሮ ከማንም ጋር ሳይነጋገርና ሳይመካከር የግፍ አገዛዙን ትንሽ መሳሪያ ይዞ ይገዘግዘዋል። አገዛዙና ህዝቡ በልህ ተያይዘው ሳይነጋገሩ ውስጥ ውስጡን ይቋሰላሉ። ማድፈት የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩ ባህል መሆኑን ያወቅኩት አሁን በስተርጅና ነው። ማድፈት መሆኑን ሳላውቅ የኢትዮጵያ ህዝብ በማድፈት የሰራውን አውቅ ነበር። እናንተም ታውቁታላችሁ። የናፒር ጦር የእንግሊዙ ጦር 32000 ነበረ። ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ። የቴዎድሮስ ጦር በናፒር ግምት 7000 ብቻ ነበረ። ናፒር 44 ዝሆኖች የዘመኑ ታንኮች ማለት ነው። ነበሩ።

[17:37]ዋናው ነገር የናፒር ጦር ዙላ አካባቢ እንደደረሰ ደጃዝማች ካህሳ ተቀብሎ መኖ እና ምግብ ለማቅረብ ለናፒር ቃል ገባለት። አካባቢው በሙሉ በጌምድርና ወሎን ጨምሮ ቴዎድሮስን ከዳው። ናፒር ሲመጣ ያደፈጠው ሁሉ አንገቱን ያንሰረሰረ ቴዎድሮስን ከዳ። ቴዎድሮስም አወቀው። ራሱን ገደለ። ናፒር ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዳልተዋጋ ያውቃል። የሸዋንም ንጉስ ሲንቁ ሲንቁ የትግሬንም ንጉስ ሲንቁ ሲንቁ ወንድ አለ ራሱ ወገድሎ የማያውቁ ተብሎ ተዘፈነለት። ከ125 አመታት ገደማ በኋላ ሻዕቢያና ወያኔ በሲአይ እርዳታ ኢትዮጵያን በወረዱ ጊዜ ወያኔ ጎጃምን በማራቶን አቋርጦ አምቦ ገባ። ከወሎ በኩል ደግሞ በመንዝ በኩል እየሮጠ አዲስ አበባ ገባ። አምቦ ገባ። መንግስቱ ሀይለ ማርያም ሀረሬ ገባ።

[19:02]ወያኔ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዳልተዋጋ ያውቃል።

[19:11]በ1886 የኢትዮጵያ ህዝብ ቴዎድሮስን ለናፒር ጦር እንዳጋለጠ በ1983 መንግስቱ ሀይለ ማርያምን ለሻዕቢያና ለወያኔ አጋለጠው።

[19:28]የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይወያይና ሳይመካከር ሳይደራጅና ሳይታጠቅ ጊዜ ጠብቆ ግፈኛውን ያጋልጣል።

[19:44]በቂምና በቀል ስሜት እየተገፋ ክፉን በክፉ የመመለስ ባህል አዳብሮ ቆይቷል። ክፉን በክፉ መመለስ ክፋትን ያራባል። ሁልጊዜም ማንኛውም ትውልድ የሚጠላው ክፋትን ነው። ግን በተፈጥሮ ሆኖ የሚጠላውን ክፋት ለማጥፋት የሚጠቀመው በሌላ ክፋት ነው። ክፋትን በሌላ ክፋት መበቀል ክፋትን መትከል ነው። ክፋት ቅምን ይወልዳል። ቅም ደግሞ ክፋትን ይወልዳል። ክፋትና ቅም ሲወላለዱ ሰላም ይደፈርሳል። ንብረት ይወድማል። የሰው ህይወት ይጠፋል። ማህበረሰቡ ቆሞ ቀር ይሆናል። ቆሞ ቀር ማህበር ማህበረሰብ መሆን ክፋትን በክፋት የመመለሱ ዋጋ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ቆሞ ቀር ሆኖ ቀረ የሚለው ጥያቄ መልስ ያገኘለት ይመስለኛል። ክፋትን በክፋት እንመልሳለን ስንል ክፋትን እያራባን ሰላምን እያጣን ቆሞ ቀር በመሆን እየተቀጣን ነው። እየተቀጣን እንቀጥላለን። ከማድፈት ቀር ሳንተዋወቅ በየክፍለ ሀገሩ ለመስክ ጥናት ስንዘዋወር ለአንድ ጥያቄ ከሁሉም ዘንድ ከኤሉባቡር እስከ ወሎ እና እስከ ሸዋ የማገኘው ተመሳሳይ መልስ በጣም ያስገርመኝ ነበር። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጊዜ ተናግሬበታለሁኝ። ጽፌበታለሁኝ። የገበሬዎቹ ማሳዎች ትናንሽ የሚሆኑት ለምንድነው። ገበሬዎች ከሚያርሱት ማሳ ጨምረው ለማረስ ምን ይቸግራቸዋል ለሚል ጥያቄ የመሬት ችግር እንዳልነበረና ከፈለጉም ሌላ ማሳ ጨምረው ማረስ እንደሚችሉ ገበሬዎቹ ይነግሩኝ ነበር። ገበሬዎቹ ጭሰኞች ከሆኑ ሌላ ማሳ በመጨመር ለባለመሬቱ የሚሰጡት ይጨምራልና መሬት ጨምሬ አላርስም ይላሉ። ለባለመሬቱ ላለመስጠት።

[22:11]አትኩሮታቸው ለባለመሬቱ በሚሰጡት ላይ እንጂ ለነሱ ለራሳቸው በሚያገኙት ላይ አልነበረም። ገበራ አራሾች ከሆኑ ደግሞ መሬት ጨምሬ ባርስ ጅብ ይጣራብኛል ይላሉ። ብዝበዛን ለመቋቋም። ጭሰኛውም ሆነ ገባሩ በሙሉ ሀይሉም ለማምረት አይፈልግም። በደፈጣ ላይ ነው። ራሱን ቢጎዳም በመለገም አጥቂውን ለመጉዳት ይፈልጋል። በደርግ ዘመን የምታስታውሱ ሰዎች ካላችሁ የደርግ የግብር ጫና በነጋዴው ላይ በጣም በበረታበት ጊዜ ነጋዴዎች የተባበሩት መንግስታት ምግብ ለስራ የሚለውን የስራ ስያሜ በመቀየር ስራ ለምግብ ብለው ሰይመውት ነበር። ብዙ ሰርተው ትርፋቸው ለከፋ ግብር የሚያዳርጋቸው እንዳይሆን ዝቅተኛውን ግብር ሲከፍሉ ሰርተው ሌላውን የስራ ጊዜ ይቅልዱበት ነበር። ስለዚህ አውቆ ምርቱን የሚቀንሰው ገበሬው ብቻ ሳይሆን ነጋዴውም ነበር ማለት ነው። ሳምሶን የድንኳኑን ምሰሶ ይዞ ውጼ ነፍሴ ምስለ ነፍሶሙ ከፍልስጤማውያን ጋር ልሙት እንዳለው ነው።

[23:42]ከተሪካችን የምንማር ከሆነ በሚከተሉት ሁለት ነጥቦች ላይ እናተኩር። የኢትዮጵያ ህዝብ ብዙ የግፍ አገዛዞችን ለመጣል ችሏል ወይም ለመጣል ረድቷል። ነገር ግን አንድም ጊዜ አዲስ የመንግስት ስርአትን ለመትከል አልሞከረም።

[24:06]በሌላ አነጋገር ከታሪካችን የምንማረው አንዱ ዋናው ቁም ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ መንቀል እንጂ መትከል የማያውቅ መሆኑን ነው።

[24:21]እነዚህን ሁለት የታሪክ እውነቶች አረጋግጠን ከተቀበልን ሁለት ጥያቄዎችን ማንሳት እንችላለን። ለኢትዮጵያ ህዝብ የግፍ አገዛዝን ለመንቀል ቀላል የሆነለት እንዴት ነው። ለኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ መንግስተ ህዝብን ለመትከል ከባድ የሆነበት እንዴት ነው። ለነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ሁላችንም የምንስማባችሁ መልሶች አሉ ይመስለኛል። የግፍ አገዛዝን መንቀል ስንል እንዳንሳሳት እያንዳንዱን የግፍ አገዛዝ ለየብቻ ማለታችን ነው እንጂ የግፍ አገዛዝን ሀሳብ እና መሰረት ከምድረ ኢትዮጵያ መንቀል ማለታችን አይደለም። ይህ ገና እስካሁንም የኢትዮጵያ ህዝብ ያልደረሰበት የአስተሳሰብ ደረጃ ነው። አሁን የምንነጋገረው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ በተወሰነ ዘመን የሚያውቀውን የግፍ አገዛዝ ለመንቀል የሚያደርገውን ጥራት ነው። መንቀሉ ቀላል የሚሆነው ብዙ የወደፊት ባለተራ ግፈኞች ሰይፋቸውን መዘው ጦራቸውን ስለውና አሰፍስፈው ጦራቸውን የሚጠብቁ ሲኖሩ ወይም የማይቻል የውጭ ሀይል ገፍጥሮ ሲመጣ ነው። እንዲህ ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅሙን ለመበቀል አጃቢ ሆኖ ነቃ ይሉ ይረዳል። ግፈኛውን ለመንቀል የተሰለፈው ሀይል ወገን ነው ወይስ ባዕድ ነው የሚል ጥያቄ አይነሳም። ምን ጊዜም ቢሆን ባዕድ ግፈኛው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በግፈኛው ላይ ይለግምበታል። አንደኛ ልዩ የሆነ ነገር አለና እንደው ሀይል ወገን እና ባዕድ አይለይም የሚለው ነገር ሁሌም እውነት አይደለም። አንድ አትሊስት እውነት አውቃለሁኝ። አንድ። የየሱስ ልጅ ዮሃንስ እያሱ በወሎ አረኛ ሆኖ በሚዋጋበት ጊዜ ኢጣሊያኖች ይልኩበት ነበር። እኛ የምንዋጋው ካንተ ጋር አይደለም። ከአባትህ ገዳይ ጋር ነው የምንዋጋው። ለኛ ገባና እናነግስሃለን እያሉ ይልኩበት ነበር። ይሄንን እውነተኛ ታሪክ ነው የነገሩኝ። አቶ ስዩም አያቆብ የሚባሉ ትምህርት ሚኒስተር ነበሩ። አንድ ሁለት ሜትር ሰውዬ። የአጋሜ ሰው ናቸው። እሳቸው ናቸው የነገሩኝ። ያዩትን ነው በእሳቸው ላይ የጣሊያን ጸሀፊ ነበሩ።

[27:26]ዮሃንስ እያሱ ሲመልስ ምን ይላል። እኔ እናንተን የምዋጋችሁ የሀይለ ስላሴ ጠላት ናቸው ብዬ አይደለም።

[27:41]እኔ እናንተን የምዋጋችሁ የኢትዮጵያ ጠላት ናችሁ ብዬ ነው።

[27:52]እያለ ነበር። ስለዚህ ነበሩ አንዳንድ ሰዎች ይመስለኛል እንደዚህ አይነት ልዩ ሀሳብ የነበረችው። ይሄ ሰውዬ እንዴት እንደሞተ የምታውቁ ሰዎች ትኖራላችሁ የሚያሳዝን ነው። መለገም ማንም የማያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀይለኛ መሳሪያ ነው። ከምሰማቸው አንዳንድ ነገሮች በኢትዮጵያ የሚሰሩ የቻይና ሰዎች ይህንን የኢትዮጵያ ህዝብ የምስጢር መሳሪያ ያወቁት ይመስላል። የፈረንጆች መለገም በድርጅት ነው። የኢትዮጵያውያን መለገም ግን ለየብቻ እና በምስጢር ነው። ሳይታወቅበት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያዳክመውን ያዳክማል። የሚያደሄየውን ያዳሄያል። የእሱ ድካምና የእሱ መደህየት ከግፈኛው ብርታትና ከግፈኛው ሀብታምና ጋር ዝምድና እንዳለው የተያያዘ እንደሆነ ያውቃል። ቀኑ ሲደርስ ታንባ ይፈርስ ነውና ተፎካካሪዎች ሲነሱ ያን ጊዜ የግፈኛው ሀብት ሲሟጠጥና ጉልበቱ ሲበረከክ የኢትዮጵያ ህዝብ ወሳኝነቱን ያረጋግጣል። የመጀመሪያውን ጥያቄ ለመመለስ ብዙም ወደኋላ ሳንሄድ ባለፉት ሀምሳ አመታት ውስጥ የመጀመሪያ አጼ ሀይለ ስላሴን የአገዛዝ ስርዓት ለመንቀል በሁለተኛ የደርግን የኮሚኒስት የተባለ ስርዓት ለመንቀል የተረባረበውን ሀይል ስናስብ የነበረውን የግፍ ስርዓት ለመንቀል ብቁ ነበር። ሁለቱንም ጊዜ ለመንቀል የተከማቸው ቅም ብዙ ነበር። እያንዳንዱ ሰው የተፈጸመበትን በደል እና ግፍ እያሰበ እሷ እንዳችም ነገር ባያደርግም ግፈኛው ሲወርድ ማየቱ ብቻ ልዩ ደስታ እየሰጠው አጃቢ መሆኑን በመሆን ይሳተፋል። አለቃ እያሉት አምሮ በአንድ አማርኛ የቅኔ ይህች ሀገር ክፉ ናት ብለዋል።

[30:08]የኢትዮጵያ ህዝብ ግፍን አይረሳም። የመበቀል ስሜቱ ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ክፋት ይመራዋል። የደረሰበትን ግፍ ሌላ ግፍ በመፈጸም ይበቀላል። እንዲሁም እያደረገ ግፍን ለሚቀጥለው ትውልድ አስታለለ። ክፋቱ ይሄ ነው። ስለ ሁለተኛው ጥያቄ ታሪካችን የሚያሳየው መንግስተ ህዝብ የመትከሉ አላማ ባለቤት እንዳልነበረው እና አሁንም እንደሌለው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በመጀመሪያ ክፉን በክፉ የመመለስን ባህር ከልቡ መንቀልና በቂም መመራትን ማቆም አለበት። ያለፈውን ግፍና ቅም ይዞ ወደፊት ወደተሻለ ሁኔታ ውስጥ እንደማይገባ ተረድቶ አይነ ልቦናውን እና አእምሮውን በወደፊቱ ኑሮ ላይ ቢያተኩር ግፍን ከስሩ ነቅሎ የህዝብ መንግስት ለመመስረት ይችላል።

[31:17]መንቀልን ቀላል የሚያደርገው የቅም ግፊት ነው። የክፋት ስሜት ነው።

[31:27]መትከልን ከኋላው የሚያገፋው ስሜት የለም። ለመትከል የሚያስፈልገው ለወደፊቱ ኑሮ የተሻለውን ሁሉ ማሰብና መመኘት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የክፋትን የቅምን እና የበቀልም መንገድ ትቶ የግለኝነትን ምስጢርን ትቶ ችግሩን ሁሉ በአደባባይ እና በግልጽ መወያየት በህብረት የመወሰን ችሎታውን በማዳበር ቢጥግነው ይረዳዋል። ለዚህ ምቹ ሁኔታ ራሱ የሚፈጥርበት ዘዴ የህብረቱ ዋና ፍሬ ሆኖ የሚከተለውን እውነተኛ መንግስት ምሰሶዎች ለመትከል የሚቻል ይሆናል። አንዱ ምሰሶ የሚለው ነፃነት ነው። ማለት ማንም ሰው የሌላውን ሰው መብት እስካልጎዳ ድረስ የፈቀደውን ነገር ለመናገር የፈለገውን ነገር ለማድረግ በፈለገው ሙያ ወይም ስራ ለመሰማራት በፈለገው አይነት ማህበር ለመደራጀት እንደ ልቡ ቁጥታውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ መንግስትን ለመሰየምና ለመሻር የግለሰብንም ሆነ የህዝብን ችሎታ የሚገልጽ ነው። ሁለተኛ እኩልነት። ማለት የኢትዮጵያን ዜጎች ሁሉ በአንድ ላይ የሚመድብና በአንድ ተርታ የሚያቆም በምንም አይነት ምክንያት ያልተዛነፉና የማይበላለጡ መብቶቹ የሚያጎናጽፍና በምንም አይነት ምክንያት ያልተዛነፉና የማይበላለጡ ግዴታዎች ያሏቸው የሀገሩ ባለቤቶች እንዲሆኑ ማረጋገጥ ነው።

[33:16]ሶስተኛ ህጋዊ ስርዓት። አንድነት የልዩነት መሳሪያ ነው። በህጋራዊ ስርዓት የልዩነት መሳሪያው ጉልበት ነው። ከህጋዊ ተሻግሮ የወጣ ማህበረሰብ ደግሞ በግለሰቦችም ይሁን በህብረቶች መሀከል ያለውንና የሚፈጠረውን ልዩነት ለማስተዳደር ህጋዊ ስርአት በግድ አስፈላጊ ይሆናል። ሰዎች በጉልበታቸው ወይም በሀብታቸው ተመክተው በሰዎች ላይ የበላይነት ለመመስረት እንዳይችሉ ህጋዊ ስርአት ያግዳቸዋል። ማንም ሰው ወይም ዜጋ በምንም ምክንያት በህግ ፊት ከሌሎች ዜጎች ሳይበልጥ እኩል ይሆናል። ህጋዊ ስርአት ባለበት ዜጎች ሁሉ በህግ ለህግ ይገዛሉ እንጂ ለሰው የማይገዙ እንዲሆኑ ህግ ይጠብቃቸዋል።

[34:14]በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገሮች ብልጭ ድርግም እያለ የሚታየው የኢትዮጵያ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን አላማ በሁለት የተለያየ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ያለ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሳይታለም የተፈተነ ነው በሀገር ውስጥ ያለውን ወያኔ ይቆጣጠረው። የብልጭታው አይሆንም የድርግግምትው ባለቤት ወያኔ ነው። ከሀገር ውጪ የሚታዩት ብልጭ ድርግምቶች የሚዘወሩት በፍቅረ ነዋይና በፍቅረ ስልጣን ነው። እኔ በእዚያ አምናለሁ። እነሱ ካልገቡበት የሌለው እንዳይሰምር እያሉ የሚፎካከሩ ቡድኖች ዛሬም አሉ። በዚያ ላይ የፈረንጅ ሀገር የኖሮ ጣጣ ጠገብነን አያውቅም። ስለዚህ ልክ በሀገር ውስጥ ወያኔ ስልጣኑን ሀብቱን በመቆጣጠር ህዝብን ለመቆጣጠር እንደሚሞክረው በውጭም ስልጣንን ሀብትን ለመቆጣጠር በመሞከር በስደተኛው ላይ ተጽኖ ይደረጋል።

[35:17]በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ንቅናቄዎች ብልጭ ድርግም የሚሉት የሚሉበት ምክንያት ይሄው ይመስለኛል። ነፃነት እኩልነትና ህጋዊ ስርአት በሀል ሰፈነበት ማህበረሰብ ውስጥ ለሀገር እና ለህዝብ የወደፊቱን እቅድ የሚቀርጸው ማነው። ከዚህ ጠያቄ የምናገኘው ፍንጭ ሰላም፣ ነፃነት፣ እኩልነት እና ህጋዊ ስርአት የማህበረሰቡ እሾህ የሌለበት ምንጣፍ ሆነው ህዝቡ እየሳቀ እንደ ልቡ ሲንከባለልባቸው አይተን ካላረጋገጥን የወደፊቱን ቤታችንን ለመካብ መጀመር የምንችል አይመስለኝም። ምንጣፉ ከእሾህ ጸድቶ እንደ ልቡ የሚያንከባለል የመሆኑ ያህል ምንጣፉ ላይ የሚንከባለሉትም ሰዎች መጽዳት ያስፈልጋቸዋል። የወደፊቱን ለመገንባት የተሰለፉ ሰዎች ባለፉት ዘመናት ከየየለበት በውድም በግድም የለቃቀሙት የምኞትና የክፋት ሸክሞች ማራገፍና አእምሮአቸውን ህሊናቸውን ማጽዳት ግዴታቸው ይሆናል ብዬ አምናለሁ።

[36:32]ትልቁ ፈተና ያለው እዚህ ላይ ነው። መድረኩ ላይ አዲስ ምንጣፍ የሚዘረጉትና የህዝቡን የክፋት እክሞች ለማራገፍ የሚያግዙት እነማን ናቸው። ለዚህ ተግባር ብቃቱ ያሏቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። እነዚህን ኢትዮጵያውያን ከየለበት አድኖ ማግኘት ከባድ ስራ ይሆናል። ነገር ግን እያንዳንዳችን ከዛሬ ወደ ነገ የሚያሽጋግረው ድልድይ ላይ ሆነን አእምሮአችንን ለመሳልና ህሊናችንን ለማጽዳት በመዘጋጀት ከባዱን ተግባር በአንዳንድ ጥያቄዎች ልናቀለው እንችላለን። ይሄንን ልለፈውና እነዚህ ጥያቄዎች በጣም አጠቃላይ ናቸው። ሲዘረዘሩ ብዙ ነገሮችን ያወጣሉ። ፍሬ ነገሩ ተደጋግሞ እንዳየው ፈረንጆች እንደሚሉት The road to hell is paved with good intentions እንዳይሆንብን ለማሳሰብ ነው። ጥሩ ማሰብ መልካም ነው። ግን ጥሩ መስራት እንደሚበልጥ አያጠራጥርም።

[37:48]ጥሩ መስራት ከራስ አልፎ ለሀገር እና ለወገን ሲሆን ደግሞ ከሁሉም የበለጠ ነው። ብዙዎቻችን ወያኔም ጭምር ፈረንጆች ሙሉ አለም ሙሉ አለም የሚለው ግሎባላይዜሽን

[38:10]በሚሉት አዲስ ፈሊጣቸው እየታለልን ነው። የራሳችን ጎጆ የራሳችንን ጎጆ ሳንጥግን ሙሉ አለም ውስጥ መግባት እንደ ወያኔ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ቢሰራም ህዝብን አደህይቶ የሚከብረው ሌላ ነው። በሙሉ አለም ለሌላው የሚከብረው የሀገሩን ባለቤት አራቁቶ ነው።

[38:46]በሙሉ አለም የሀብታሞቹ የትኛውም ሀገር ባለቤት ሲሆኑ ድሃዎቹ ሀገራቸውንም የሚያጡበት ሁኔታ ነው። ነገር ግን አንድ ቀን የባሪያዎች ነፃነት ሳይታወጅ ይፈነዳል። ዛሬ ትርፍራፊ የያዙ ባሪያዎች አለቃ በመሆን የሌላቸው ሰዎች ያኔ መሬት ተከፍታ ብዋጠኝ ይላሉ። ከዚህ ህዝባዊ መቅሰፍት መዳን የሚቻለው ዛሬ ነው። የእኛ ትንሽ አለም ጠፍታ ሙሉ አለም አትለማልምም። ወደኋላ እያዩ ወደፊት መሄድ አይቻልም። ቅም በትናንቱ የጥላቻ ስሜት ተቀስፎ አእምሮ እንዴት ብሎ የነገውን ተስፋ ይወጠናል። ስሜትን ቀስፎ የያዘውና ከወደኋላ ጎልቶ የሚታየው በቀል ነው። ጥፋት ነው። ድብድብ ነው። ይህንን የተፈጥሮ የእንስሳ ስሜት መቆጣጠር ሳይቻል በምን ሀይል እንዴት ተብሎ ወደፊት ለማየትና ልማትና እድገትን ማሰብ ይቻላል። ወደኋላ ማየት ቆሞ ለመቅረት መወሰን ነው።

[40:03]ወደፊት ማየት ለመገንባት ነው። ለውጥን ፈልጎ ቅምን ለመበቀል መሰማራት ከታሪክ አለመማር ነው። ዛሬ በየቤቱ በሹክሹክታ የሚወራ የኢትዮጵያ ጉዳይ አለ። የትግሬዎች ጉዳይ።

[40:26]ትግሬዎች ለብቻቸው እንደ ግል ጉዳያቸው አድርገው በሹክሹክታ ያወራሉ። ትግሬ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንም በሹክሹክታ ስለ ትግሬዎች ያወራሉ። ለምንድነው ይህንን ብሄራዊ ጉዳይ በግልጽ እና በአደባባይ የማንወያይበት። ምክንያቱ ግልጽ ነው። በሁለቱም በኩል በትግሬዎችም ሆነ ትግሬ ባልሆኑት በኩል ሸር ስላለ ነው። ያልጸዳ አስተሳሰብና ያልጸዳ መንፈስ ስላለ ነው። በሁለቱም በኩል ልዩነትን የበላይነት መሰላል በማድረግ ለመጠቀም ነው።

[41:11]በሁለቱም በኩል ምንም አይነት የበላይነት መሰላል ዘለቀይታ እንደሌለውና ሁሉንም በአፍጥሞ እንደሚደፋው ያለፈው 40 አመት አስተምሯል።

[41:26]ዋናው ከታሪካችን የምናገኘው ትምህርት እያንዳንዳችን ራሳችንን ለማሸነፍ መወሰንን ነው። እያንዳንዳችን ራሳችንን ለእውነት ለፍጥ ለነፃነት ለእኩልነትና ለአብሮነት ማስገዛትን ነው። በግልጽነትና በመወያየት በመተሳሰብና በመተባበር የሚያገኙትን ጥቅም የዕለት ድርግምት አድርገን ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን ማስተላለፍ ይጠበቅብናል።

[42:02]በታሪካችን የምንቆጭበትን ሁሉ እኛና የሚቀጥሉት ትውልዶች እንዳይደግሙት ሁልጊዜ ወደኋላ እያየን ከመቆጨት እና ከንፈርን ከመንከስ እንዳን። የወደፊት ኢትዮጵያን የምንገነባው በጥብ ሳይሆን በስምምነት በንትርክ ሳይሆን በወይይት በጉልበት ሳይሆን በብልሃት በጨለሌነት ሳይሆን በእውቀት በስሜት ሳይሆን በአህዛብ እየተሞራረድን ነው። የወደፊት ኢትዮጵያን የምንገነባው አብረን የምንኖርበትና አብረን የምናድግበት የጋራ ማህበረሰብ ለመፍጠርና ለመቅረስ ክፋትን በክፋት ከመመለስ ጋር በሀሌም በገበሬም ስንለያየን የወደፊት ኢትዮጵያን የምንገነባው አንድ በመሆን አይደለም። በመለያየትም አይደለም። ልዩነታችንን በአንድነት አቅልበን በጋራ ስምምነት ስናስራቸው

Need another transcript?

Paste any YouTube URL to get a clean transcript in seconds.

Get a Transcript